የአፋር ክልል በወያኔ አይን፣ የይህደጎ እና የቡራህ አባ ጉርብትና በአብዓላ!

የአፋር ክልል በወያኔ አይን፣ የይህደጎ እና የቡራህ አባ ጉርብትና በአብዓላ!

0 749


የአፋር ክልል በወያኔ አይን፣ የይህደጎ እና የቡራህ አባ ጉርብትና በአብዓላ!

በአካደር ኢብራሂም ( Akku )

ያው እንደ ተባለው የአፋር ክልል ከደርግ ውድቀት በኃላ በኢትዮጲያ ውስጥ ከተፈጠሩ ዘጠኝ ክልሎች አንዱ ነው።

ምንም እንኳን የአፋር ክልል በተባለው መሰረት በመልከዓ ምድር አቀማመጥ፣ በቋንቋ ተናጋሪዎች አሰፋፈር እንዲሁም በባህል ላይ የተመሰረተ አከላለል ሙሉ ለሙሉ ተጠቃሚ ባይሆንም የአፋር ክልል እየተባልን የሄው ሩብ ምዕተ አመት ቆጥረናል።

ምንም እንኳን በግሌ በሔር በህረ ሰቦች እራስን በራስ ማስተዳደር ወይም በሌላ አባባል የፌደራሊዝም ደጋፊ ብሆንም፤ ወያኔ ላንዱ እናት ላንዱ ደግሞ የእንጀራ እናት የሆነው የተወሳሰበ አከላለልና ህዝብን ሊያባላ ጫፍ ላይ የደረሰው ሰርዓት ግን አስፈርቶኛል።

በአሁኑ ግዜ የኢትዮጲያ ህዝቦች አንድ አንባገነንን ከማስወገድ ይልቅ እርስ በእርስ ሲጋጩ እናስትውላለን።

የዚህ መንስኤው ደግሞ የመንግስት ፖሊሲ ውጤት መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።

ቆየት ያሉትን ወደ ጎን ትተን የትናንቱን በማንሳት ወደ ዋናው መልዕክተ ልግባ።

ወልቃይቴው እኔ አማራ ነኝ እንጂ የትግሬ ማንነት አልፈልግም ብሎ በግልጽ ሲናገር፣ አይ ማንነትህን እኔ ነው የማውቅልህ በማለት ጨፍልቀው ለማለፍ ሲሞከር መላው ጎንደር ተንሰቶ፣ ሳያበቃ መላው አማራ ገንፍሎ ወያነ ለጥቅት አምልጦ በስቸኳይ ግዜ አዋጅ ወይም በህመም ማስታገሻ እየመራን መሆኑን ይታወቃል።

ገና ወደ ተሟላ ጤንነቱ ሳይመለስ የአፋርንም መሬት አምሮኛል በማለት አብዓላ የትግራይ ናት የሚለው ጥያቄ ከወያኔነት አልፎ የትግራይነት መልክ እየያዘ ይገኛል።

የጽሁፌን አርዕስት የይህደጎ እና የቡራህ አባ ጉርብትና በ አብዓላ ላይ ያልኩበት ምክንያትና ትርጉሙን ላካፍላችሁ መሰለኝ፣ ይሕደጎ የትግረኛ የሰው ስም ሲሆን ትርጉሙ ይንጠቀው ውይም ነጣቂ እንደማለት ነው።

ቡራህ አባ ማለት ደግሞ የአፋር ስም ሲሆን ትርጉሙ ባለ ቤት ማለት ነው።

ሪዕሱን የመርጥኩበት ምክንያት መገመት ባይከብዳችሁም ነጣቂው እና ባለ ቤት መቼም ተስማምተው ሊኖሩ አይችሉም።

አብዓላ የሚባለው ከተማ አፋርን ከትግራይ ክልል ጋር የሚዋሰኑ ወረዳዎችን ማለትም የስምንት ወርዳዎች ዋና ከተማ ስትሆን ከተማዋ ከመቀለ 45 ኪሎ መትር ርቀት ላይ ትገኛለች።

በነግራችን ላይ እነዚህ ስምንት ወረዳዎች ለስሙ የአፋር ይባሉ እንጂ በተዘዋዋሪ የትግራይ ክልል ወይም የሕዋሃት የጎሮ አትክልት ከሆኑ ቆይተዋል።

አንድ መታወቅ ያለበት ነገር እነዚህ ወረዳዎች ዝም ብለው ወረዳዎች ብቻ አይደሉም።

መቀሌ የተገነባችው በአስዓሌ አሞለ ጨው ሲሆን አስዓሌ የምትገኝበት የባርህሌ ወርዳ፣ የመላው ኢትዮጲያ የጨው ምንጭ የሆነው አፍደራ፣ የአለም አስገራሚ ዳሉል፣ኤርታ አሌ፣ ፖታሽ፣ የኮናባ የማያልቀው ወርቅና ማዓድን እና ሌላም የተፈጥሮ ሃብት የሚገኝበት ወረዳዎች ናቸው።

ካሁን በፊትም በያንዳንዱ ወርዳዎች በዚህ ነጣቂው እና ቡራህ አባ ማሃል በተደረገው ጦርነት የብዙ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል።

አሁን ደግሞ በጦርነት ያልቻሉትን ነጠቃ በእጅ አዙር ከወሰዱ በኃላ አብዓላን የወያኔ ሰርዓት ሳያበቃ በፊት ወደ ትግራይ ለማካለል የሚደረግ ሩጫ ይመስላል።

በእርግጥ አብዓላን ሸኽት ሰላሉ ብቻ አቤት ብላ መቀሌ አትገባም።

ይህን ያልኩበት ምክንያት ምንም እንኳን በተደራጀ መልኩ ባይሆንም ለአብዓላ ህዎቱን ለመስጠት የተዘጋጀ ወጣት መኖሩን ልብ ብያለሁ።

የአብዓላን ወደ ትግራይ ማካለል ጥያቄ ወይም በሌላ አባባል እንደተባለው እዛ የሚኖሩ የትግረኛ ተናጋሪዎች ልዩ ወረዳ እንዲሰጣቸው የተነሳው ጥያቄ ትንሽ የቆየ ቢሆንም አሁን በቅርብ ግዜ የሚታዩት የትግራይና የአፍር ግጭቶች ለየት ያለ ይመስላል።

አንዳንዶቹ በክልሉ አፋረኛ የስራና የትምህርት ቋንቋ እየሆነ ሰለመጣ አፋረኛ ሰለማይችሉ ወይም ሰለማይፈልጉ በትግረኛ እንዲማሩና እንዲሰሩ የራሳቸው ልዩ ወረዳ እንዲሰጣቸው የሚደረግ እንቅስቃሰ ነው ይላሉ።

እኔን ጨምሮ ሌሎቻችን ደግሞ ደግሞ የሄ ምክንያት ብቻ ሳይሆን የወያነ ሰርዓት ከማብቃቱ በፊት የነጠቁትን መሬት ህጋዊ ለማድረግ የሚደረግ ሩጫ ነው ብለን እናምናለን።

ያም ሆነ ይህ ዋናው ነገር አሁን በኢትዮጲያ ውስጥ በየቦታው የሚነሱ የማንነት እና የድምበር ይገባኛል ግጭቶች የወኔ ብልሹ ሰርዓት ውጤት መሆኑን ብዞዎቻችን ይሚንስማማበት ነጥብ ይመስለኛል።

ወያኔ እራሳችሁን በራሳችህ አስተዳድሩ ቢልም ሙሉ በሙሉ እራስን የማስተዳደር መብት አለመስተቱ አንዱ የችግሮች መንስኤ ነው ብዬ አምናለሁ።

ካሁን በፊት በ 2014 በኮኮናባ ወርዳ አንድ የኮሌጅ ተማሪ በትግራይ ሚሊሻዎች የተገደለበት ግጭት አሁን አብዓላ ላይ የምናየው ግጭት ቀጣይ አካል ነው።

ኮናባ ወረዳ አዓላ ስር ከሚተዳደሩ ስምንት ወረዳዎች አንዷ ስትሆን እዛ አከባቢ የድምበር ይገባኛል ግጭት ተፈጥሮ አንድ አብደላ እድሪስ የሚባል የኮሌጅ ተማሪ የሆነ ወጣት በትግራይ ክልል ተጣቂ ምሊሻዎች ተመቶ መሞቱ ይታወቃል።

ይህን ላስታውስ የፈለኩበት ምክንያት በዛን ግዜ በትግራይ በኩል የውቅሮ ዞን አስተዳደር የሆኑት ሰው በግልጽ ለአፋር ሽማግለዎች የተናገሩት ነገር ላካፍላችህ ፈልጌ ነው።

የዛኔ ልጁ ከሞተ በኃላ የሁለቱም ክልሎች መሪዎች ከሁለቱም ክልሎች

የአገር ሽማግሌዎች የተካፈሉበት ሰብሰባ በውቅሮ ከተማ አድርገው ነበረ።

ለግዜው ስማቸውን የማላስታውሰው የዞኑ አስተዳደር እናንተ በኢትዮጲያ ምንም መሬት የላችሁም አርፋችሁ ካልተቀመጣቹህ ወደመጣችሁበት እንመልሳችሃለን ብለው ነበረ።

ታዲያ ዛሬ አብዓላ ወደ ትግራይ እንድትካለል መጠየቃቸው ምን ይገርማል ለማለት ፈልጌ ነው።

የሚገርመው ወያኔ የትግራይ ህዝብ ጥያቄ እያስመሰለ የሚያራምደው የመሬት ወረራ ባሰበው መሰረት በትግራይ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እያስገኘለት ቢመስልም፣ ትርፉ የትግራይ ህዝብ ታሪካዊ ጥላት ከማብዛት የዘለለ ይሆናል ብዬ አላሳብም።

ለምሳሌ በትግራይ ውስጥ ራሱ ሦስት ቀበሌዎች በግዴታ ወደ ትግራይ እንዲካለሉ ተደርጓል።

እኛ አፋሮች ነን እንጂ ትግሬነት እንድጫንብን አንፈልግም በማለትለ25 አመታት ያለ መንግስታዊ መሰረተ ልማት የሚተዳደሩ የሳውኔ አፋሮችን ጭምሮ እነ ታላክ፣ ሰሔሎ፣ ጎዶሌ፣ ወደ አፋር መካለል የነበረባቸው ወይም የአፋረኛ ተናጋሪዎች፣ በታሪክም ሆነ በመልከዓ ምድር የአፋር ክልል ቢሆኑም ወያኔ ሰላልፈለገ ብቻ ያለ ባህላቸው፣ ያለ ቋንቋቸው፣ በአጠቃላይ ከማንነታቸው ውጭ እየኖሩ ይገኛሉ።

ይህን ጉዳይ ያነሳሁበት ምክንያት አሁን ወያኔ የሚያራምደው ወረራ ትግራይ ውስጥ ወያነን እንቃወማለን ብለው የተደረጁ ድሪጅቶች ሳይቀሩ ሲደግፉ ይታያሉ።

ካሁን በፊት ወልቃይት የማን ናት የሚለውን ጥያቄ ከአመሪካ ድምጽ ራዲያ የቀረባላቸው የዓረና ትግራይ ሊቀመምበር አቶ አብራሃ ደስታ የሰጡት መልስ ወደ ህወሓት ፊላጎት የሚያዘነብል ነበረ።

አቶ አብራሃ ደስታ ጥያቄ ያነሳው ህዝብ እስከሆነ ድርስ የወልቃይት ህዝብ ድምፀውሳኔ ማድረግ አለበት ብለው ተናግሯል።

በሌላ በኩል ወልቃይት ላይ ኣሁን ከሌላ የትግራይ አከባቢ ለስራ የመጡ ሰዎች ቁጥር ከትክክለኛ ወልቃይቴው ሰለመበልጥ ህዝበ ውሳኔ አያዋጣንም የሚሉ ስዎች አስተያየት አንብቤ ነበር።

ልክ አሁን በአፋር ክልል አብዓላ ወረዳ ላይ ልዩ ወረዳ ይሰጠን የሚሉት የትግራይ ተወላጆች ለስራ፣ ለንግድ መጥተው እንደቀሩት በየ ሱቁ የእኛ ቋንቋ ሰለተነገረ ልዩ ወረዳ እንፈልጋለን፣ በከተማው ላይ ትግረኛ ተናጋሪ ሰለበዛ መሬቱ የእኛ ነው የሚለው ጥያቄ እንዳነሱት።

በአፋር ክልል የማን ብሔር ተወላጅ ነህ፣ ምን አይነት ቋንቋ ተናገራለህ፣ ሳይባሉ ከብዙ ብሔር ብሔረ ሰቦችና ከሌላ አከባቢ የመጡ ኢትዮጲያዊያን ይኖራሉ።

ይህ ማለት ግን ኢትዮጲያዊያን በመሆናቸው በምነኛው ቦታ መኖር ይችላሉ ማለት እንጂ ዘር እየቆጠሩ ህዝቦችን ማጋጨት አይደለም፦

ከአንድ ወር በፊት አብራሃ ደስታ በፈይስቡክ ገፁ ላይ አብዓላ የትግራይ እንደሆነችና እዛ የሚኖሩ ትግሬዎች መብታቸው ተነፍገው እየታገሉ መሆኑን ምስክርነቱን ሰጥቷል።

በነገራችን ላይ አብዓላ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እዛው በአብዓላ ወረዳ ምክረ ቤት 3 ተወካዮች አላቸው።

የትምህርት፣ የስራ፣ የጤና እና ሌሎች አገልግሎቶችን ከአፋሮችም በላይ ይጠቀማሉ።

ታዲያ አብራሃ ደስታ እውነት የማንነት እና የመብት ተሟጋች ከሆነ ለአመታት ሰውኔ ላይ ምንም አይነት መሰርተ ልማት ሳይኖራቸው በስቃይና በግፍ እየኖሩ ላሉት አፋሮች ለመብታቸው መከበር ለሚያድርጉት ትግል ለምን አንድ ቃል አልተነፈሰም ?

እኮ ለምን! ?

አሁን ባለፈው ማክሰኞ በዛው አብዓላ ከተማ የተፈጠረው ግጭት የወዴፊቱን ሁኔታ የሚያማላክት ነው።

ሆነ ብለው የሃይማኖት ቦታ ወይም መስገጃ ቦታ ላይ የሙዚቃ ድግስ ዝግጅት አታዘጋጁብን፣ ከፈለገችሁ ሌላ ቦታ ላይ አድርጉ ሰላሉ ብቻ አፋሮች በጥይት ተደብድበዋል።

ለነገሩ ባለ ቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች አይደል የሚባለው?

ማንም ሰው እንደ ሰው መብቱ ሊከበርለት ይገባል የሚል እምነት ቢኖረኝም ያንዱን መብት ተጨፍልቆ ያንዱን መብት እንዲከበር መጠየቅ አብሮ የመኖርን ባህል ማዛባት ብቻ ሳይሆን ሊቀረፍ የማይችል ቁርሾ ያስክትላል።

እንደ እኔ አስተያየት በሰላም ማንም ሰው አብዓላ ላይም ሆነ መቀሌ ላይ ቢኖር ችግር የለብኝም።

ግን ቤቴ እንድትኖር ሰለፈቀድኩልህ መጠቅለል ካማረህ ያኔ ጠብ መነሳቱ አይቀርም።

ጠብ ከተነሳ ደግሞ ለሁሉም አይበጀም፣ በተለይ በተለይ ለአገር አደገኛ ነው።

መጥታችሁ በከፈታችሁት ውስጥ ሱቅ ትግርኛ ልንናገር እንችል ይሆናል፣ ግን መሬቴንና ሃይማኖቴን ከነካህብኝ በሰላም መኖር ያስቸግረናል ይሕደጎ ዓርከይ።

Comments

comments