የአፋርና አጎራባች ክልሎች ግጭቶች – ከአካደር ኢብራሂም (Akku )

የአፋርና አጎራባች ክልሎች ግጭቶች – ከአካደር ኢብራሂም (Akku )

0 690

አንድ ደጀኔ አሰፋ የተባለው ግለሰብ በፌስቡክ ገጹ ላይ እልባት ያጣውና የተካረረው የራያ ህዝብና የአፋር አጎራባች ወረዳዎች ግጭት በሚል ርዕስ አንድ ጹሁፍ ጽፎ አይቼ ነበር።

አቶ ደጀኔ አሰፋ ጉዳዩን ለዘመናት የቆየ መሆኑን እና በግጦሽ መሬት፣ ከብት ዘረፋና መሰል ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እንደነበር ጥናቶች ቢመሰክሩም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እንደ መንስኤነት የሚጠቀሱት ከወትሮው እየተለየና ፖለቲካዊ ይዘት እየያዘ መምጣቱን አመላካች ነገሮች ያሉ ይመስላሉ፦ ይላሉ አቶ ደጀኔ።

ይሁን እንጂ አቶ ደጀኔ ፖለቲካዊ መልክ እየያዘ ነው ያሉት በዝርዝር ምን ዓይነት ፖለቲካ እንደሆነ ባያስቀመጡም እኔም ይህንን ጦረነት በተቻለ መጠን መከታተል ሞክረያለሁና ምናልባትም ፖለቲካዊ መልክ ያዘ የሚያስብል ነገር ቢኖር ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በትግራይና አፋር አጎራባች አከባቢዎች የሚደረጉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በትግራይ በኩል የሚዋጉት ሲቪል የለበሱ የልዩ ሃይልና የመከላኪያ ታጣቂዎች መሆናቸው ራሱን የቻለ አስፈሪ ፖለቲካ ነው ማለት ይቻላል።

በተለያዩ ግዜያቶች በአፋርና ትግራይ ክልል ድንበሮች ላይ በሚደረጉ ግጭቶች የአፋር አርብቶ አደሮች እንደሚሉት እየገደሉን ያሉት የመንግስት መሳራያ የታጠቁ የልዩ ሃይል አባላትና የአከባቢ ሚሊሻ ወታደሮች ናቸው በማለት ይከሳሉ።

አቶ ደጀኔ አሰፋ ከ 1988ጀምሮ አፋሮች ወደ ራያ መንደሮችና ቀበሌዎች በመውረድ የተመረጡ ግለሰቦችን የመግደል ሁናቴ መስተዋሉን ታማኝ ምንጮች ይመሰክራሉ ካሉ በኃላ ከትግራይ በኩል የአፀፋ ምላሽ እንኳን እንዳይሰጡ በመንግስት ታቅበው ቆይተዋል ይላሉ።

ታዲያ በአቶ ደጀኔ በኩል ያሉ ታማኝ ምንጮች አፋሮችን እንደ ወራሪና ሽፍታ አድርገው ሰላማዊ ሰዎችን እየመረጡ የሚገድሉ አድርገው ማቅረብ ከሆነ ታማኝነት ለእኔ ከዚህ በላይ ሞጥፎ ፖለቲካ የለም።

መንግስት ያስታጠቃቸው ፖሊሶችና ሚሊሻዎች በይፋ በሚሳተፉበት ጦረነት አፀፋ ምላሽ እንኳን እንዳንስጥ በመንግስት ታቅበናል ማለትም በጣም የተጋነነና ግጭቱን ሊያባብስ እንጂ ሊያስታረቅ የማይችል የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ነው።

አቶ ደጀኔ በጹሁፋቸው ደስታ ጉማራ በ1976.ም በርሃ የወጣ ነባር ታጋይ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ትጥቅ ፈትቶ ሰላማዊ ኑሮ ሲመራ የነበረና በአካባቢው ነዋሪ የነበረ ያሉት ግለሰብ አቶ ደጀኔ እንዳሉት ተመርጦ ሳይሆን የተገድለው በአከባቢው አፋሮች በደም ሲፈለግ የነበረና በተደጋጋሚ ለህግ እንዲ ቀርብላቸው ቢጠይቁም ሰሚ አጥተው እንደቆዩ መሆኑን ይነገራል።

ባጠቃላይ በዚህና መሰል ግጭቶች በሁሉም በኩል የሚያልፈው የሰው ህይዎት፣ የሚዘረፈው ንብረትና ህዝብ ማሃል በሚጠፋው ሰላም ዋና ተጠያቂ ሊሆን ይሚችለው አገረቷን እያስተዳደረ ይሚገኘው መንግስት መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል።

በትግራይና በአፋር አጎራባች ወረዳዎች ቢቻ ሳይሆን በአጣቃልይ በሁሉም ክልሎች ማሃል፣ በተለይ ደግሞ በአፋር እና በአጎራባች ክልሎች ማሃል እየተከሱቱ ያሉ ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ከሚሟገቱ ሰዎች አንዱ ቢሆንም መፍትሄው ግን አሁን አቶ ደጀኔ በጻፉት አይነት ህዝብን ይበልጥ እርስበርስ እንዲጋጭ የሚያነሳሱ ቀስቀሳዎች ሳይሆኑ ታሪክና ጥናት ላይ የተመሰረተ ፍትሃዊ አካለልን ማስፈጸም፤ ፍትሃዊ አስተዳርና ህዝብ ማሃል ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ውህደትና ውይይት

( integration) በመፍጠር፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የአገር ሺማግለዎች በማወያየት ምናልባትም ዘላቂ መፍትሄ ሊመጣ ይችል ይሆናል።

ይሁን እንጂ ከዚህ መንገድ ይልቅ ህዝብን የማጋጭትና አንዱን በማስታጠቅና ሌላው ላይ ማዝመት ከሆነ ጉዳዩ ከዚህ በላይ እየተካረረና ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል።

ፍትህ ይስፈን ዘረኝነት ይውደም!

Comments

comments