የአብዓላ ልዩ ወረዳ ጥያቄና ከጀርባ ያለው ህቡዕ አጀንዳ Cammadí Macammad

የአብዓላ ልዩ ወረዳ ጥያቄና ከጀርባ ያለው ህቡዕ አጀንዳ Cammadí Macammad

0 484

የአብዓላ ልዩ ወረዳ ጥያቄና ከጀርባ ያለው ህቡዕ አጀንዳ
(Cammadí Macammad)
ክፍል አንድ
እንደ መነሻ
አፋሮች ለኢትዬጵያ ብሎም ለቀንድ አፍሪካ የድንበር ዘብ ሆኖ ለዘመናት ያገለገለ ህዝብ መሆኑን ታሪክ ይመሰክራል። የልቦለድ ታሪክ “ደራስያን” እውቅና ባይሰጧቸውም።
የአፋር መሬት ከተጎሪ እስከ ዘይለዕ የተዘረጋው የቀይባህር ወደቦች ያቀፈ መሆኑና የአለማችን ትላልቅ የንግድ መርከቦች የሚያልፍበት ባባል መንደብን በጓያ መያዙ ጂኦ ፖለቲካዊ ተመራጭነቱ የአለም ኃያል መንግስታት ትኩረት መሳቡ ለአፋር ህዝብ ጥቅም ከመስጠት ይልቅ ለጉዳት ዳርጓቸዋል ማለት ይቻላል። ለዛም ነው ከውጪም ከውስጥም ጠላት የበዛባቸውና፣ ጠላትን በመመከት ስራ ተጠምዶ ከአካባቢው ምቹነት አንፃር እዙህ ግባ የሚባል ስልጣኔ ለአለም ልያበረከቱ ያልቻሉት። (የለም ማለት ግን አይደለም፣ በሚፈለገው ደረጃ አለመሆኑ እንጅ።)
በሌላ በኩል አፋሮች ከቁጥራቸው ጋር ስነፃፀር በጣም ሰፊ መሬት ሰላላቸውና መሬቱ ካለው ተፈላጊነት አንፃር ጠላት ሰለሚበዛባቸው ጠላትን ለመመከት ብዙ ዘዴዎች መፍጠር የቻሉ ስሆን “የጎሳ አወቃቀር፣ የአካባቢ ደህንነት የሚያጣሩበት የኢንፎርሜሽን መረብ (ዳጉ)፣ እንድሁም ሁሉም ሰው፣ ሁል ግዜ የሙሉ ግዜ ወታደር እንድሆን በማድረግ ትጥቅ ባህላቸውን ማድረግ” ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
የጎሳ አወቃቀር ያስፈለገበት ምክንያት የአፋር መሬት ሰፊ መሆኑን የህዝቡ ውስንነት ባንድ ማዕከላዊ መንግስት ስር ዳር ድንበሩን መጠበቅ አዳጋች በመሆኑ ነው። የጎሳ አወቃቀር ስባል ከላይ ወደ ታች የሚወርድ የስልጣን ሰንስለት ሳይሆን በአግድም የሚዘረጋ (Horizontal structure) ሲስተም ነው። አሰራሩ ሁሉም ጎሳ ባለበት አካባቢ ባላባት ስኖራቸው፣ ሁሉም ባላባቶች ደግሞ እኩል ስልጣን አላቸው። ያ ማለት የጎሳ ባላባቶች በሚያስተዳደሩበት አካባቢ እንደ ዳኛም እንደ ጦር መሪም ይሰራል ማለት ነው። በዚህ መሰረት ጠላት በየተኛውም አቅጣጫ ብመጣ በቀላሉ የሚመከቱበት ሁኔታ ይፈጠራል ማለት ነው። ባላባቶቹ እነደ ጠላት ጥንካሬ ይተጋገዛሉ። (ሱልጣን የሁሉም ባላባቶች የበላይ ሆኖ እንደ ማዕከላዊ መንግስት ይሰራል። )
(1) የአብዓላ ጉዳይ
1,1 ከታሪክ አንፃር
አብዓላ እንደ ማንኛውም የአፋር መሬት በጎሳ ባላባት ትተዳደር ነበር። እንደ ሌሎቹ የአፋር አካባቢዊች ከጎረቤት (እንዳርታ፣ ወጀራት) ወረራ ይካሄድባታል። እንደ ሌሎቹ ጠላትን በመመከት አይታሙም።
አፄ ዩሃንስ “ያየኔ ኢትዬጵያ” ንጉስ ነግስት ሆኖ ስሾም አብዓላ “ያኩሚ (Yaakumi) የሚባል የመላ ሄርቶ ጎሳ (certoh Affaraf) ባላባት ትተዳደር ነበር። የአብዓላ መሬት አቀማመጥ ለወታደራዊ ስልጠና ምቹ መሆኑን የተረዳው አፄ ዩሃንስ “መሬቱን ለስልጠና ሰለሚፈልግ ፍቀድልኝ” ብሎ ወደ ያኩሚ መልዕክት ላከ። ያኩሚ በበኩሉ “መሬቱ የመላ አፋር እንጅ እኔ ለብቻዬ የሚወስነው የለኝምና አማክራቸው መልስ እሰጠሃለሁ።” ብሎ ላከበት። በዚህ የተናደደው አፄ ዩሃንስ “ማንንም ሳታስቀሩ ጨፍጭፏቸው።” በማለት ትዕዛዝ አስተላለፈ።”ሽኸቱ” በማለት። ትግሬዎች አብዓላን “ሸኸት” ማለት የጀመሩት በዛ የአፄ ዩሃንስ የጭካኔ ትዕዛዝ ነው።
ያኩሚ በበኩሉ የንጉሱን ወታደር የሚገዳደር የተደራጀ ሃይል ባይኖረውም ለጠላት መንበረከክ ባህሉ አልነበረምና በጀግንነት ተፋለማቸው። ከ39 ሺ እስከ 43 ሺ የሚገመት ህዝብ በጦርነቱ ተሰዋ። በመጨረሻ ያኩሚ በጀግንነት ስፋለም ቆይቶ “ኡርኩዲ” በሚባል ስፍራ ተሰዋ። የያኩሚ ሴት ልጅ የሆነችው “ዳቶ” ቆንጆ ሰለነበረች አፄ ዩሃንስ ለራሱ አገባት።
በመጨረሻም “ምት” ወደ መተማ ስጠራው “ስመለስ ክርስትናን ያልተቀበለ ባገኝ አልምረውም።” ብሎ ዛተባቸው። አፋሮቹም “ወይ አንተ አትመለስ ይሆናል። ወይ እኛ አንቆይ ይሆናል።” በማለት መለሱለት። እንዳሉም አልተመለሰም። ህዝቡም ተገላገለ። በንደዚህ አይነት ሁኔታ እስከ ደርግ ዘለቁ።
,
~ በደርግ ዘመን አፋሮች በአምስት የተለያዩ ግዛት ስር ተካለሉ። ብሆንም ግን መሬታቸውን ለማንም አሳልፈን አንሰጥም በማለታቸው አካባቢያቸውን በራሳቸው እንድያስተዳደሩ ተደረገ። በተመሳሳይ አብዓላን “ዓባስ አብድላ” ያስታዳድራት ነበር። ከሳቸው በኋላም ሀጂ እብራህም እስከ ህልፈታቸው አስተዳድሯታል።
,
~ እንደሚታወቀው በደረግ አገዛዝ ስር የደረሰባቸው ጭቆና በመቃወም ለ17 አመታት መራራ ትግል ስያካህዱ “በአንድ አስተዳደር ስር ቋንቋቸውን፣ ባህላቸው በአጠቃላይ ማንነታቸው” በማስከበር ነበር። የደርግ አገዛዝ ተገርስሶ ኢህአዴግ ስመጣ ተቀዳሚ አላማው “የብሔር ብሔርሰቦች ጥያቄ” መመለስ በመሆኑ፣ አወቃቀሩ ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገ ሳይሆን ባህልንም፣የጋራ ሰነልቦናን ጭምር የሚያካትት ክልላዊ አወቃቀር ነው።
~ እዚ ጋ አንድ መስማማት ያለብን ነገር አለ። እሱም “የአፋር ክልል” ተብሎ አፋር እንደ ክልል ስዋቀር: በመጀመሪያ ደረጃ የታገሉለት አላማ መሆኑን ነው። በሁለተኛ ደረጃ የታገሉለት ኣላማ “ማንነታቸውን ማስከበር” መሆኑን ነው።
አፋር ደግሞ ማንነቱ “አፋሬ (Qafarre)” በሚባል መሰሶ ላይ የተመሰረተ ነው። አፋሬ ማለት “የአፋር” ማለት ስሆን በውስጡ “የአፋረኛ ቋንቋ፣ የአፋር ባህል፣ የአፋር ማድዓ(ህግ) እንድሁም የአፋር መሬትን” ያካተተ ነው። ስለዚህ ዓፋር እንደ ክልል ስቋቋም እነዚህ አራት መሰረታዊ ነገሮች መነሻ በማድረግ ነው ማለት ነው።
በዚህ መነሻ አፋሮች፣ አፋርኛን እንደ ስራ ቋንቋ፣ ባህልን እንደ መለያ፣ የአፋር ህግን እንደ መዳኛ፣ እንድሁም የአፋር መሬትን እንደ መኖሪያ በመያዝ “የአፋር ክልል” ተብሎ በአምስት ዞኖች ተዋቀረ ማለት ነው።
ስለዚህ የአፋር መሬት ከአፋር ማንነት ተነጥሎ የማይታይ “የአፋርነት” አንዱ መለያ ነው ማለት ነው።
*******
1,2 የችግሩ መነሻ
አብዓላ ላይ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጥያቄ ስነሳ: መነሻችን ልሆን የሚችለው 1983 ነው። ከዛ በፊት የነበረው ከላይ እንደተገለፀው ነው።
ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት አፋር እንደ ክልል ስቋቋም አብዓላ የዞን 2 ዋና ከተማ ሆና ተመረጠች። ያኔ ታዳ ከ20 ቤተሰብ የማይበልጡ የትግራይ ተወላጆች ይኖሩባት ነበር። እነሱም ለአፋሮች የእርሻ ማሳ ሰለሚጠብቁላቸው ነው።
የሚገርመው ነገር “ወደ ትግራይ ተመለሱ” ስባሉ: “ኣይ! እኛ ካሁን በኋላ ወደ ትግራይ አንመለስም። ከአፋሮች ጋር ሰለተዛመድን እዚህ ይሻለናል።” አሉ። የተወሰኑ ሰዎች ግን ወደ ኩሓ እና መቐለ ተመልሷል።
አፋሮቹ በበኩላቸው “እነሱ በእረሻ ስራ ከኛ የተሻለ ልምድ ሰላላቸው ከእኛ ጋር ብሰሩ ደስ ይለናል።” አሉ። ተፈቀደላቸውም።
ከዛ ግዜ ጀምሮ ከአፋሮች ጋር በወንድማማችነት ይኖሩ ነበሩ። በዚህ መሃል “ለስራ ፍለጋ፣ ለንግድ እንድሁም ለቤተሰብ ጥየቃ” በሚል ብዙ የትግራይ ተወላጆች ወደ አብዓላ ገቡ። ያኔ ወደ ኩሓና መቐለ ተመልሶ የነበሩም ጭምር ተመልሶ መጡ።
እንደሚታወቀው የአፋር መሬት በተፈጥሮ ሀብት አይታማም። ይበልጥ ደግሞ ዞን ሁለት። የሄን ሀብት የያዘ መሬት ወደ አፋር ክልል መካለሉ ያልተዋጠላቸው ብዙ ታጋዬች ነበሩ። እነ ስዬ አብረሃ ከፊት ይሰለፋሉ።
እነዚህ ታጋዬች በታሪክም በህግም የሄንን መሬት ወደ ትግራይ መመለስ እንደማይችሉ ስያረጋገጡ መላ ዘየዱ። የቁጥር ጨዋታ። በተለያዩ ምክንያት ይገቡ የነበሩትን ብቻ ሳይሆን በልዩ ሁኔታ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ወደ ዞን ሁለት ወረዳዎች (በስሩ 8 ወረዳዎች ይገኛሉ።) በገፍ መግባት ጀመሩ። አፋሮቹ ተንኮል አላሰቡምና እንድነግዱ ብቻ ሳይሆን እንድኖሩም ፈቀዱላቸው።
*እነሱ በሚፈልጉት ደረጃ ማሰፈራቸውን ካረጋገጡ በኋላ የመብት ጥያቄዊችን መጠየቅ ጀመሩ። በርግጥ ባይጠይቁም የተነፈጉ መብት አልነበረም። ማንኛውም ነዋሪ በሚኖርበት አካባቢ ማገኘት የሚገባውን መብት ማገኘታቸውን ካረጋገጡ በኋላ በህቡዕ መደራጀት ጀመሩ። ከአንዳንድ የመንግስት አካላትና ታጋዬች ጋር በመተባበር ለሁለት ዓመት የማሳመን ስራ ካከናወኑ በኋላ በ2001/2 በግልፅ የልዩ ወረዳ ይሰጠን ጥያቄ ለወረዳ ም/ቤት አቀረቡ። ከዛ ዞን፣ ከዞን ክልል ደረስ አደረሱ።
ጥያቄው ለክልል ም/ቤት ቀርቦ ከተመረመረ በኋላ የተወሰኑ ቡድኖች የሚያራምዱ አጀንዳ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ተቀባይነት እንደሌለው አሳወቋቸው። አሁንም አልቆሙም። ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት አደረሱ። ፌዴሬሽኑ ወረዳው በአፋር ክልል ስር የሚገኝ በመሆኑ ውሳኔውን መስጠት የሚችሉት የአፋር ክልል መሆኑን ነገሯቸው። በዛ ሳይወስኑ ከ3 ወር በፊት ከም/ቤቱ የተወጣጡ ልዑካን ቡድን በመላክ የጥያቄውን ተገቢነት እንድመረመረ ተደርጓል። በተደረገው ምርመራም “የተጠየቀው ጥያቄ እና መሬት ላይ ያለው እውነት የማይገናኝ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ህቡዕ አጀንዳ ያላቸው ሰዎች የሚያረምዱት መሰረት የሌለው ጥያቄ መሆኑን” ለህዝብ ተናገረው ተመለሱ።
**
ይቀጥላል,,,

Comments

comments