የአብዓላ ልዩ ወረዳ ጥያቄና ከጀርባ ያለው ህቡዕ አጀንዳ ( Cammadí Macammad...

የአብዓላ ልዩ ወረዳ ጥያቄና ከጀርባ ያለው ህቡዕ አጀንዳ ( Cammadí Macammad ) የመጨረሻ ክፍል

0 923

የአብዓላ ልዩ ወረዳ ጥያቄና ከጀርባ ያለው ህቡዕ አጀንዳ
(Cammadí Macammad)
የመጨረሻ ክፍል
በክፍል አንድ እንደተገለፀው የልዩ ወረዳ ጥያቄ ተቀባይነት እንደማያገኝ ስያረጋገጡ የትግል ስልቱን ቀየሩት። ጥያቄያችን የማንነት ነው በማለት። ብሆንም ለጥያቄያቸው የሚያቀርቡት መከራከሪያ አሁንም ወደ ቀድሞ ትግል የሚያዘነብል መሆኑ የትግል አቅጣጫቸውን ቀየሩ እንጅ በማንነት በኩል በመሽሎክ የልዩ ወረዳ ጥያቄ ወይም ወደ ትግራይ የማካለል ላይ ለማረፍ መሆኑን ቀላሉ መረዳት ይቻላል።

የሚያነሱት ጥያቄ ከሞላ ጎደል ሦስት ናቸው።
****
1ኛ:አብዓላ በደርግ ዘመን በትግሬ ግዛት ስር ትተዳደር ሰለነበረ የትግራይ አካል ናት።
2ኛ: የአብዓላ ነዋሪዎች አብዘኞቹ (ቁጥር በመጥቀስ) ትግረኛ ተናጋረዎች በመሆናቸው ወደ ትግራይ መካለል ስገባቸው ህውሓት በሰራው ስህተት ወደ አፋር እንድካለል ተደርጓል።
3ኛ: የአፋር ክልል የትምህርት ፖሊሲ በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገው “የኤሌሜንታሪ ት/ት በአፋርኛ መስጠቱ” ውሳኔ ትግረኛ ተናጋሪ የሆነው የትግራይ ተወላጆችን ታሳቢ ያላደረገ ውሳኔ በመሆኑ ተማሪዎቹ በቋንቋቸው (ትግረኛ) እንድማሩ በማድረግ ማንነታቸው ልከበርላቸው ይገባል። የሚሉ ናቸው።
***
~ እዚህ ጋር በግልፅ እንደተቀመጠው ጥያቄያቸው የአብዓላ ጥያቄ እንጅ የመብት ጥያቄ እንዳልሆነ ነው። አንድ በ አንድ ለማየት እንሞክር።
1ኛ: “አብዓላ በትግራይ ግዛት ስር ነበረች” ካሉ፣ የደርግ ስርዓት ይከተል የነበረው አከላል ብሔርን መሰረት ያደረገ አልነበረም። በዚህም አፋር በ5 ግዛት ስር ተበትና ነበር ማለት ነው። ስለዚህ ያኔ በትግራይ ተካሎ የነበሩ 5 ወረዳዎች የትግራይ ነው ካልን የአፋር የሚባል መሬት ላይኖር ነው ማለት ነው። ምክንያቱም ያኔ የአፋር ግዛት የሚባል ሰላልነበረ። በዛ ከሄድን አሰብም ልመለስ ነው ማለት ነው?! .
2ኛ: አብዛኛው ነዋሪዎች ትግረኛ ተናጋሪ ነቸው የሚለው መሰረት የሌለው ቀደዳ ብሆንም: እነሱ እንደሚሉት በአብዓላ ከተማ የሚኖር ህዝብ አብዛኛው ትግረኛ ተናጋሪ በመሆናቸው “ወደ ትግራይ ይካለል” ወይም “ልዩ ወረዳ ይሁን” ከተባለ: በአብዘኛው የአፋር ከተሞች ላይ (አይሳኢታ፣ አዋሽ፣ ሎጊያ፣ ሰመራ) ከአፋርኛ ተናጋሪዎች ይልቅ የአማርኛ ወይም የትግረኛ ተናጋሪዎች ቁጥር ይበዛል። ታዳ በዚህ አካሄዳቸው የአፋር የሚባል ከተማ ላይኖር ነው ማለት ነው። የክልሉ ዋና ከተማም ወደ ትግራይ ይካለል ልሉ ነው ማለት ነው? 85% በገጠር የሚኖረው ማህበረሰብ በከተማ ቁጥራቸው ትንሽ ነው በማለት “ለእንጄራ ፍለጋ” የመጣ ሰው “ልዩ ወረዳ” ልሰጥ ነው?
.
3ኛ: ትግረኛ ተናጋሪዎች በትግረኛ ነው መማር ያለባቸው ከተባለ፣ በአብዓላ ከተማ የሚገኙ ከ 3 የማይበልጥ ኤሌሜንተሪ ት/ቤቶች የትግራይ እና የአፋር ተብሎ ይከፋፈል እያሉን ነው? እነሱ በየቀኑ ትግራይን ለቆ ወደ አፋር በገቡ ቁጥር የትምህርት ፖሊሲ እንድከለስላቸው ያሻሉን?
በነገራችን ላይ እስካለፈው ዓመት ደረስ አፋሮች በራሳቸው ቋንቋ ተምረው አያውቁም። ታዳ የአፋር ተማሪዎች ጉዳይ ሰለማይመለክተን የትግራይ ተማሪዎች ጥያቄ ይመለስ ካሉ፣ እኛም የናንተ ጉዳይ አይመለከተንምና ትግረኛ መቀለ ላይ ተማሩ የማለት ግዴታ አለብን። ምክንያቱም ጎራ ለይቷልና።
በሌላ በኩል ደግሞ በትግረኛ ብቻ እንማር ካሉ ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ት/ቱ የሚሰጠው በአማርኛ እና በእንግልዘኛ ነው። እሱንም አንማርም ልሉ ነው? (በዚህ አጋጣሚ አፋርኛን ለመማር ፍላጎት የለንም እያሉ መሆኑን ለማስታወስ እንፈልጋለን።)
በዚህ ተባለ በዛ፣ ጥያቄው “አልሸሹም ዞር አሉ” ነው። ወደ ዋናው ጥያቄ የሚያደረስ ድልድይ ነው።
***
1,3 ያሁኑ የተማሪዎች ጉዳይ
ከሦስት ሳምንት በፊት የአብዓላ ሁለተኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት ተማሪዎች ከሆኑት የትግራይ ተወላጆች መካከል 6 ወንዶች በት/ት ቤት ዩኒፎርማቸው ላይ “ተጋዳላይ” የሚል ፅሁፍ፣ 5 ሴቶች ደግሞ “በሶ” የሚል ፅፎ በመግባታቸው የት/ቤቱ ዳይሬክተርና ም/ዳይሬክተር የተማረዎቹን ቤተሰብ በማስጠራት መክሯቸው በማስጠንቀቂያ እንድታለፉ ተደርጎ ነበር።
በዚህ ውሳኔ የተበሳጨው አንድ ተማሪ ወደ ዳይሬክተሩ በመሄድ “ከዛሬ ጀምሮ ጅልባብ የለበሱ ሴቶችና ሱሪ የቆረጡ ወንዶች እዚህ ግቢ ውስጥ እንድገቡ አንፈቅድም።” በማለት የብዙ ተማሪ ጥያቄ አስመስሎ አቀረበ። ዳይሬክተሩም “የሄ ጥያቄ ከመጀመሪያ ኬዝ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው መሆኑ ብቻ ሳይሆን አንተ ያቀረብከው ጉዳይ የግለሰቦች የሃይማኖት ነፃነት የሚጋፋ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም” በማለት መለሰለት።
በማግስቱ ልጁ ከሌሎች ጓደኞች ጋር በመሆን የት/ቤቱ ሽንት ቤትና ግድግዳ ላይ የእስልምና ሃይማኖትና አፋርን የሚሰድብ ፅሁፍ መፃፍ ጀመረ። በዚህ የተናደዱ የአፋር ተማሪዎች “ጉዳዩን በፍጥነት አጣርታችሁ ውሳኔ እንድሰጥበት እንፈልጋለን” በማለት ለዳይሬክተሩ ጥያቄ አቀረቡ።
የት/ት ቤቱ የድስፕልን ኮሜቴ ከዞኑ ፖሊስና ፍትህ አካላት ጋር በመሆን ጉዳዩን ስያጣሩ “የልዩ ወረዳ ጥያቄ” ያነገቡ መሆናቸውን ደረሱባቸው።
በመሆኑም በማስጠንቀቂያ ታልፎ የነበሩ 11 ተማሪዎችና “ፊዳካ” የሚል ፅሁፍ በዩኒፎርማቸው ላይ የፃፉ ሁለት ሴቶች ለአንድ አመት ከት/ት ገበታ እንድታገዱ ተወሰነ።
***
እንግድህ እነ አብረሃ ደስታ “የመብት ተሟጋቾች” ብሎ የሚጠራቸው እነዚህ 11 ተማሪዎች ስሆኑ የቀሩት 2 ተማሪዎች አፋር በመሆናቸው ዘሏቸዋል።
በዚህ ፅሁፍ ለማብራራት እንደተሞከረው በአብዓላ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያጡ መብት ኑሯቸው ሳይሆን በነ ስዬ አብረሃና በአብረሃ ደስታ ፊታውራሪነት ዞን ሁለትን ወደ ትግራይ የመጠቅለል ዘመቻ አንድ አካል ነው። ዘመቻው በአብዘኛው በዓረና አባላት የሚደገፍ ስሆን በመላ ትግራይ ዘንድም ተቀባይነት ያገኘ ሰፊ ፖሮጄክት ነው።
***
1.4:መደምደሚያ
የእንዳርታ መሳፊንቶች አብዓላን መውረር የሁል ግዜ ስራቸው በነበረ ግዜ፣ የአንድ ጀግና ሚስት ከሩቅ አየቻቸው። ወደ በሏ በመሄድም “የልጆቼ አባት: አብረሃ አጥር ዘለለ” ብላ ነገረችው። ባሏም “አብረሃ አጥርን የሚዘለው ከልጆቻችን ልጆች አሉት ወይስ ከግመሎቻችን ግመል አለው?” በማለት ተነስቶ ሂዶ እንደአመጣታቸው መለሳቸው ይባላል።
እኔ ደግሞ “አብረሃ ሆይ: አብዓላን የሚትመኘው ከልጆቻችን ልጆች አለህ ወይስ ከመሬታችን መሬት አለህ?” በማለት ፅሁፌን ዘጋሁ።

Wagariy Maqaane ( ዋጋሪይ ማዓኔ! )

Comments

comments