በአፋር ክልል በመብረቅ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአፋር ክልል በመብረቅ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

0 759

በአፋር ክልል በመብረቅ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአፋር ክልል በመብረቅ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

ሲ) በአፋር ክልል ሁለት ወረዳዎች በደረሰ የመብረቅ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባባሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

መብረቁ አራት የቤት እንስሳትን መግደሉንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ተወካይ አቶ ከድር አብደላ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት፥ የመብረቅ አደጋው የደረሰው በክልሉ ጭፍራ እና እዋ በተባሉ ሁለት ወረዳዎች ነው።

ከትናንት በስቲያ ማታ በእዋ ወረዳ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ድረስ የጣለውን ዝናብ ተከትሎ በቦሎቶሞና ቤሉ በተባሉ ቀበሌዎች የወደቀ መብረቅ ሁለት ሰዎችና ሁለት የቀንድ ከብቶችን ሲገድል በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት አድርሷል።

በዚሁ ቀን ጭፍራ ወረዳ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3፡00 ሰዓት በጣለው ዝናብ ተገሪ፣ አስኮማና ጭፍራ 01 በተባሉ ቀበሌዎች መብረቅ ወድቆ አራት ሰዎችንና ሁለት የቀንድ ከብቶችን መግደሉን ተናግረዋል።

በተያዘው የክረምት ወራት በክልሉ ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ በተለያዩ ወረዳዎች ተደጋጋሚ የመብረቅ አደጋ መከሰቱንም አቶ ከድር አስታውሰዋል።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በዱብቲ፣ ኩነባና ጭፍራ ወረዳዎች ተመሳሳይ የመብረቅ አደጋ ደርሶ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉንም በማሳያነት ጠቅሰዋል።

በአጠቃላይ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በመብረቅ ተመተው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 13 ደርሷል።

 

Comments

comments